USB Flash Drive እንዴት bootable ማድረግ እንችላለን?

USB Flash Drive እንዴት bootable ማድረግ እንችላለን?

አንድ ፍላሽ operating system ሲጫንበት bootable ሆነ እንላለን። 
bootable የሆነ ፍላሽ ብዙ ጥቅም ያለው ሲሆን ከነዚህ መካከል

  • ኮምፒውተራችን ላይ አዲስ operating system ለመጫን
  • የረሳነውን የwindows password ለማለፍ
  • የተበላሸ ወይም ክራሽ ያደረገ ዊንዶስ ለማስተካከል
  • ፍላሹ ላይ የተጫነውን operating system ቀጥታ (Live) ለመጠቀም 

ፍላሻችንን bootable የምናደርግባቸው የተለያዩ ዘዴዎች ያሉ ሲሆን ከነዚህ መካከል

  1. በተለያዩ bootable ማድረጊያ ሶፍትዌሮች ለምሳሌ rufus, Universal installer, UNetBootin, etc
  2. በwindows ኮማንድ ፕሮፕት (CMD)

ለዛሬ በuniversal installer አፕሊኬሽን እንዴት በቀላሉ ፍላሻችንን bootable እንደምናደርግ እናያለን።

የሚያስፈልጉን ነገሮች
1. በትንሹ 8GB የመያዝ አቅም ያለው ፍላሽ
2 Universal installer አፕሊኬችን (ሴታፑን ከታች አስቀምጬላችኋለሁ)
3. የምንጭነው ሙሉ ኦፕሬቲንግ ሲስተም setup (Windows 7, 10, kali Linux, Ubuntu...etc)

0) Universal USB installerን ክሊክ አድርጋችሁ ክፈቱትና የምትጭኑትን operating system አይነት ምረጡለት።
1) የምትፈልጉትን Operating system browse አድርጋችሁ ጫኑ።
2,3) ፍላሻችሁን ምረጡለትና create በሉት።

4) process አድርጎ እስኪጨርስ ጠብቁትና ሲጨርስ close ብላችሁ ፍላሻችሁን ንቀሉ።

ከላይ ያሉትን በትክክል ከተከተላችሁ ፍላሻችሁ Bootable ይሆናል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow