Save ሳናደርግ የጠፋብንን word ዶክመንት እንዴት መልሰን እናገኛለን?

Save ሳናደርግ የጠፋብንን word ዶክመንት እንዴት መልሰን እናገኛለን?

Microsoft word ዶክመንት ስንሰራ ድንገት save ሳናደርግ የምንሰራው ነገር ቢጠፋብን መልሰን ለማግኘት የምንችልባቸው መንገዶችን ላሳያችሁ።
ከዛ በፊት ግን እኛ እያስታወስን save ማድረግ የምንረሳ ከሆነ በራሱ automatically save እንዲያደርግልን ማድረግ እንችላለን። 
ሌላኛውም ምናልባት ኮምፒውተራችን ከinternet ጋር የተገናኘ ከሆነ OneDrive ላይ እንዲያስቀምጥልን ማድረግ አለብን። Google drive በነጻ 5GB storage ስለሚሰጠን microsoft.com ላይ በመግባት አካውንት ከከፈትን በኋላ word ላይ የምንሰራውን ዶክመንት automatically  በቀጥታ ወደ አካውንታችን save እንዲሆን ማድረግ እንችላለን።

ይህንን ቀድመን ማስተካከል

  1. Microsoft Word ከከፈታችሁ በኋላ File የሚለውን ትነካላችሁ።
  2. Options ምረጡ።
  3. Save
    ▪️ autosave OneDrive and  SharePoint online files by default on word የሚለውንና check box on አድርጉ።
    ▪️ Save AutoRecovery information የሚለውን አማራጭ ደግሞ የautorecovery ጊዜውን 1 minute አድርጉት።

AutoRecovery file location በdefault C:\Users\big\AppData\Roaming\Microsoft\Word\ ውስጥ ታገኙታላችሁ ነገር ግን የፈለጋችሁትን ፎልደር መምረጥ ትችላላችሁ።

በዚህ መሰረት ካስተካከላችሁ በኋላ ድንገት save ሳታደርጉት ከጠፋ መልሳችሁ ለማግኘት

  1. file ትመርጣላችሁ
  2. Open
  3. ታች ላይ Recover Unsaved Documents የሚል አማራጭ አለላችሁ እሱን በመምረጥ መክፈት ትችላላችሁ።

ከላይ የተዘረዘሩትን አማራጮች ሳትሞሉ ፋይላችሁ ከጠፋ አንድ ተጨማሪ አማራጭ ላሳያችሁ።
.asd የmicrosoft default file recovery extension ነው።

File explorer ትከፍቱና ሰርች ባሩ ላይ ሄዳችሁ .asd ብላችሁ search ታደርጋላችሁ።
recover ለማድረግ ብዙ ጊዜ ስለሚፈልግ ምንም ነገር ሳትነካኩ እስከሚጨርስ ትጠብቁታላችሁ።
ሲጨርስ right click አድርጋችሁ በword ክፈቱት።

ከላይ በተዘረዘሩት መንገዶች ካልተመለሰ 3rd party ሶፍትዌሮችን መጠቀም ይኖርባችኋል።
ለምሳሌ recuva, EaseUS, AnyRecover

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow