2-step verification ምንድን ነው? እንዴትስ እንጠቀመዋለን?

2-step verification ምንድን ነው? እንዴትስ እንጠቀመዋለን?

እንደሚታወቀው በማንኛውም website ወይም application ላይ account ከከፈትን በኋላ username  እና password አስገብተን login ማድረግ እንችላለን። ነገር ግን username እና password ብቻውን አስተማማኝ ስላልሆነና ለ3ኛ ወገን ተጋላጭ ስለሚያደርገን ብዙ ድርጅቶች ተጨማሪ  የsecurity  step ይጨምራሉ። ስለዚህ ሃከሩ ዩሰርኔምና እና ፓስዎርዳችን ቢኖረው ራሱ login ለማድረግ ተጨማሪውን step ማለፍ ይጠበቅበታል። ይህ ተጨማሪ ሁለትም ሆነ ከዛ በላይ security feature  2-step verification ይባላል። ከ2 በላይ ከሆነ ደግሞ multi step verification/authentication ይባላል።
ይህም የsecurity ደረጃውን ከፍ ለማድረግና access የሚያደርገው ትክክለኛ ባለቤቱ መሆኑን ለማረጋገጥ ያግዛል። 
አሁን አሁን ሁሉም ሶሺያል ሚዲያዎች ማለት ይቻላል 2-step/multi step verification አላቸው። ስለዚህ ያሉንን ሶሻል ሚዲያዎች 2 step verification "on" ማድረግ አለብን።

 የተለያዩ የ2 step verification አይነቶች አሉ።

  • Biometrics (ልዩ የሰውነት ክፍል የሚጠይቁ): ለምሳሌ እንደ ጣት አሻራና የፊት ገፅታ፤ እነዚህ የverification አይነቶች አብዛኛውን ጊዜ የምንጠቀማቸው ስልክ ላይ ሲሆን የተሻለ የsecurity ደረጃ አላቸው።
  • የስልክ ቁጥርና ሲም ካርድ የሚጠይቁ: እነዚህ የverification አይነቶች ደግሞ usernameና password ከሞላን በኋላ በተጨማሪ ኮድ በስልክ ቁጥራችን ይላክልናል። እንደ ቴሌብር አይነቶች ደግሞ አካውንት የከፈትንበትን ሲም ካርድ ስልካችን ውስጥ ካላስገባን የማይሰሩም አካውንቶችም አሉ።
  • Email
  • physical card

የተወሰኑ social media  ፕላትፎርሞችን በሚከተለው መንገድ two step verification on ማድረግ ትችላላችሁ።

  • Telegram
    Setting - privacy and security - Two step verification
  • Instagram 
    setting - security - two factor authentication
  • Facebook
    Setting - security and login - use 2 factor authentication
  • TikTok
    Setting and privacy - security - 2 step verification

እዚጋ መታወቅ ያለበት ነገር 2 step verification ስላለው ብቻ 100% secure ነው ማለት አይደለም። "አለም ላይ 100% secure የሆነ ነገር የለም!!" ስለዚህ ሌሎች ተጨማሪ የsecurity መንገዶችን መጠቀም ይገባል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow