AI

chatGPT አካውንት እንዴት መክፈት እንችላለን?

chatGPT, openAI በተባለ ድርጅት የተሰራ Large Language Model (LLM) ውስጥ የሚካተት Generative ai ነው። በሌላ አማርኛ ማሽን ወይም ኮምፒውተር ሲሆን እስከ 2021 ድረስ ያለውን የአለም መረጃ ከተሰጠው በኋላ ሰዎች የሚጠይቁትን ማንኛውንም ነገር ልክ እንደሰው ሆኖ ሰዎች በሚገባቸው መልኩ አቀናብሮ የሚመልስልን ማሽን ነው።

  • ማንኛውንም ጥያቄ ይመልሳል።
  • ማንኛውንም ፅሁፍ ይፅፋል፣ ያብራራል።
  • መማር የምንፈልገውን ነገር ያስተምራል።

በአጠቃላይ እኛ የምንፈልገውን ማንኛውንም መረጃ በትክክል መጠየቅ ከቻልን ለሁሉም ነገር ግልፅ በሆነ አማርኛ መልስ ይሰጣል። ምን አለፋችሁ የማያውቀው ነገር የለም ማለት ይቻላል።

ChatGPT እንዴት መጠቀም እንችላለን?

chatGPT ለመጠቀም የግድ አካውንት መክፈት ይኖርብናል።
አካውንት አከፋፈቱ በቅደም ተከተል ይህን ይመስላል።

  • chat.openai.com ላይ ትገቡና signup የሚለውን click ታደርጋላችሁ።

  • ኢሜላችሁን አስገቡና continue በሉት። ወይም በGoogle, Microsoftና በApple አካውንታችሁም መግባት ትችላላችሁ።

  • ኢሜላችሁን verify እንድታደርጉ ይጠይቃችኋል ገብታችሁ verify አድርጉ።
  • ስማችሁንና የልደት ቀናችሁን ሞልታችሁ Agree ትሉታላችሁ።

  • የሚሰጣችሁን captcha በትክክል ከሞላችሁ account በትክክል ከፍታችኋል።

  • ስልክ ቁጥር ከጠየቃችሁ ቁጥራችሁን አስገቡለትና verification code እስከሚገባ ጠብቃችሁ ስታስገቡት ይሰራል።
    አካውንት ለመክፈት ደግሞ ልክ እንደቴሌግራም ስልክ ቁጥር ያስፈልገናል። emailና ስልክ ቁጥር ካስገባን በኋላ ባለ 4 digit verification code ወደስልኩ ይልካል። ያንን ኮድ የጠየቀን ቦታ ላይ ስናስገባ ትክክል ከሆነ የአካውንት ባለቤት እንሆናለን ማለት ነው። 

This site uses cookies. By continuing to browse the site you are agreeing to our use of cookies Find out more here