ኮምፒውተራችንን በምንከፍትበት ግዜ የምንሰማው ቢፕ ድምፅ (Beep sound) ምንድን ነው?

ኮምፒውተራችንን በምንከፍትበት ግዜ የምንሰማው ቢፕ ድምፅ ምንድን ነው?
ማንኛውንም ተዘግቶ የቆየ ኮምፒውተር የፓዎር ቁልፉን ተጭነን በምንከፍትበት ግዜ የመጀመርያው ሂደት POST (Power-On-Self-Test) ይባላል። ተጠቃሚው ፒሲውን ባበራ ቁጥር ባዮሱ(BIOS) ዋና ዋና የኮምፒውተር ክፍሎች በትክክል መስራታቸውን ለማረጋገጥ መረጃ በማሰባሰብ ልዩ የምርመራ ሙከራ ያደርጋል። ይህ ሂደት Power On Self Test ይባላል። አጠቃላይ ሂደቱ በጣም አጭር ጊዜ የሚወስድና የተወሳሰበ ቢሆንም ኮምፒውተራችሁን በምታበሩበት ጊዜ ማውዝና ኪቦርዳችሁ ብልጭ ብሎ ሲጠፋ ሌሎች የኮምፒውተር ክፍሎችም አጭር ምልክት ሲያሳዩ መመልከት ይቻላል።
BIOS በዚህ ሙከራ ሂደት ላይ አንዳች የሃርድዌር ችግርን ካገኘ POSTCODE ተብሎ በሚጠራው ሞኒተሩ ላይ የስህተት መልእክት ያሳያል። ነገር ግን ማንኛውም የምስል ወይም የፅሁፍ ምልክት ከመላኩ በፊት ችግሩ ከተከሰተ ምስላዊ በሆነ ምልክት ሊያሳየን አይችልም ወይም እስክሪናችን ላይ ምንም አይነት display አይመጣም። ስለዚህ ስለችግሩ ኮምፒውተራችን ሊነግረን የሚችልበት ብቸኛው አማራጭ ድምፅ መጠቀም ይሆናል።
የኮምፒውተራችን ባዮስ ያገኘውን ችግር በድምፅ መልኩ ተጠቃሚው ሊረዳው በሚችልበት beep ወደሚል ድምፅ ይለውጠዋል።
የBeep ኮዶች ከBIOS BIOS የተለያዩ ሊሆኑ ስለሚችሉ ምን ማለት እንደሆነ በትክክል ለማወቅ ትንሽ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።
በአጠቃላይ ግን አንድ ፈጣን ድምጽ (one quick beep) ካሰማ ሁሉም ነገር በትክክል እየሰራ ነው ማለት ነው።
ነገር ግን ከዚች ብቸኛ ትንሽ beep ከምትል ድምፅ ሌላ ተጨማሪ ድምፅ ከሰማን የቢፕ ኮድን ለማዎቅና በኮምፒውተሩ ላይ ያለውን ችግር ለመረዳት የኮምፒውተር ማዘርቦርዱን ማንዋል ማየት ሊኖርብን ይችላል።
ኮምፒውተሮች የተለያየ የቢፕ ድምፅ ርዝማኔ ሲኖራቸው አንዳንዶቹ በጣም አጭር፣ አንዳንዶቹ ረጅም አንዳንዶቹ ደግሞ የተለያየ ድምጽ ሊኖራቸው ይችላል። ያ ማለት በሁለት የተለያዩ ኮምፒውተሮች ላይ ያለው ተመሳሳይ የቢፕ ድምጽ ሙሉ ለሙሉ የተለያዩ ችግሮችን ለመግለጽ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል ማለት ነው።
እነዚህን የኮምፒዩተር ቢፕ ኮዶች ለማወቅ የተሻለው መንገድ ምንድነው?
ቀደም ሲል እንደገለጽነው የቢፕ ኮድ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ ቀላሉ መንገድ ባዮስ ቢፕ ኮድ ለእያንዳንዱ ቦርድ እና የኮምፒውተር አይነት የተለየ ስለሆነ የማዘርቦርድ ማንዋል መመልከት ይኖርብናል። ነገር ግን በዚህ ዘመን የሚያጋጥሙንን ችግሮች ያላቸውን ቢፕ ኮድ ማዘርቦርድ ሰሪዎች በማዘርቦርድ ማኑዋላቸው ውስጥ አይዘረዝሩም። ለምሳሌ እንደ ASUS Z690 አይነት ኮምፒውተሮች የማዘርቦርድ ማንዋላቸውን ብንመለከት ስለ ቢፕ ኮድ የሚገልፅ ነገር አናገኝም።
በአጠቃላይ ብዙ ኮምፒውተሮች የሚያሰሙት የቢፕ ኮድ ብዛትና የችግሩ አይነት መፍትሄው ከታች የተዘረዘረውን ይመስላል።
1 Beep - Refresh Failure - Reseat/replace memory, troubleshoot motherboard.
2 Beeps - Parity Error - Reseat/replace memory, troubleshoot motherboard.
3 Beeps - Memory Error - (first 64KB) Reseat/replace memory.
4 Beeps - Timer Failure - Troubleshoot motherboard.
5 Beeps - Processor Failure - Troubleshoot CPU, motherboard.
6 Beeps - Keyboard Controller Failure - Troubleshoot keyboard, motherboard.
7 Beeps - Virtual Mode Exception Error - Troubleshoot CPU, motherboard.
8 Beeps - Display Memory Failure - Trouleshoot graphics card, motherboard.
9 Beeps - ROM BIOS Checksum Failure - Replace ROM BIOS, troubleshoot motherboard.
10 Beeps - CMOS Shutdown Register Failure - Troubleshoot motherboard.
11 Beeps - L2 Cache Failure - Troubleshoot L2 cache, motherboard.
What's Your Reaction?






