ሰሞኑን ያጋጠመው CrowdStrike IT outage ምንድን ነው?

ላለፉት ቀናት ብዙ ባንኮች፣ አየር መንገዶች፣ በዓለም ዙሪያ ያሉ ቢሮዎች በኮምፒውተር ስርዐታቸው ብልሽት ምክንያት ስራቸው በመስተጓጎሉ ብዙ ሰዎች ለእንግልት እነርሱም ለኪሳራ ተዳርገዋል። የWindows 10 ኮምፒውተራቸው Blue screen of Death (BSOD) ውስጥ በመግባቱና በትክክል መነሳት ባለመቻሉ ይህ ነገር ሊያጋጥማቸው ችሏል።
BSOD ምንድን ነው?
The Blue Screen of Death (BSOD) ማለት አንድ Windows OS የተጫነበት ኮምፒውተር ከፍተኛ የሲስተም ችግር ሲያጋጥመውና ያ ችግር ተጨማሪ ከፍተኛ ችግር ከማስከተሉ በፊት ማስተካከያ ሳይደረግለት እንዳይሰራ የኮምፒውተሩን ሙሉ ስራዎች የሚያቋርጥበት መንገድ ነው።
አንድ ኮምፒውተር BSOD በሚያጋጥመው ጊዜ blue screen በማብራት ስለገጠመው ችግር ዝርዝር መረጃ ስክሪኑ ላይ ያስነብባል።
ከዊንዶውስ 7 እና ከዛ በፊት የነበሩ ኮምፒውተሮች BSOD በሚያጋጥማቸው ጊዜ ተጠቃሚዎች በሚረዱት ቋንቋ ስለችግሩ የተወሰነ ፅሁፍ ያሳያሉ። ከWindows 8 በኋላ ግን ተሻሽሎ ዝርዝር መረጃ ያሳያል። ለበለጠ መረጃም ስክሪኑ ላይ ያለውን QR code በስልካችን scan በማድረግ ስለችግሩ የበለጠ ማዎቅ እንችላለን።
አንድ ኮምፒውተር BSOD mode ውስጥ ሲገባ ችግሩን በራሱ ማስተካከል (automatic troubleshooting) ይሞክራል። በዚህ ጊዜ በተደጋጋሚ በራሱ restart ሊያደርግ ይችላል። ችግሩን በራሱ መፍታት ካልቻለ manual troubleshooting ያስፈልገዋል። ይህም የተጫኑ አዲስ ድራይቨሮች ካሉ እነሱን ወደቀድሞ version መመለስ፣ የBIOS update ካለ እሱን ቼክ ማድረግ ወይም የሃርድዌር ችግር ካለ እሱን መፈተሽ ይኖርብናል።
የBSOD ችግር ምክንያቶች ብዙ ናቸው ከነዚህ ውስጥ
⚫Faulty hardware: Problems with critical hardware components such as the graphics card, sound card, SSDs (solid-state drives), or RAM (memory).
⚫Low disk space: የC:/ drive መሙላት የኮምፒውተሩ operating system በትክክል እንዳይነሳ ስለሚያደርገው BSOD ውስጥ ሊገባ ይችላል።
⚫Malware: malicious የሆኑ ሶፍትዌሮች ሲስተም ፋይሎችን corrupt ሊያደርጓቸው ስለሚችሉ BSOD ውስጥ ይገባል።
ሰሞኑን ያጋጠመው IT outage ምንድን ነው?
CrowedStrike የተባለው የሳይበር ሴኩሪቲ ካምፓኒ የWindows ኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ የሚጫን falcon የሚባል ሶፍትዌር አለው።
ይህ Falcon software ኮምፒውተሮችን ከሳይበር ጥቃት የሚከላከል ሲሆን አዲስ update ሲኖር ራሱን automatically update ያደርጋል።
የሰሞኑ IT outage የተከሰተው በዚህ update ምክንያት ነው።
ይህን ለማስተካከል CrowedStrike እየሰራ እንደሆነ ቢናገርም በትክክል ይህ ነው የሚባል መፍትሄ እስካሁን አላሳወቀም።
ነገር ግን ችግሩ ያጋጠማቸው ተጠቃሚዎች በዚህ መልኩ በራሳቸው ማስተካከል ይችላሉ።
✔️1. Boot Windows into Safe Mode or WRE.
✔️2. Go to C\Windows\System32\drivers\CrowdStrike
✔️3. Locate and delete file matching "C-00000291*.sys"
✔️4. Boot normally.
What's Your Reaction?






