የስልካችሁ ስክሪን ቢሰበር ፋይላችሁን እንዴት ማግኘት ትችላላችሁ?

ስልካችሁን ከኮምፒውተራችሁ ጋር connect አድርጋችሁ የስልካችሁን screen display ለማድረግን እንዲሁም ስልካችሁን ሙሉ በሙሉ በኮምፒውተራችሁ ለመቆጣጠር የሚጠቅማችሁ ቀላል ሶፍትዌር ላሳያችሁ።
Scrcpy ይባላል። ኮምፒውተራችሁ ላይ የሚጫን ሶፍትዌር ሲሆን ስልካችሁ ላይ ግን ምንም አይነት አፕሊኬሽን መጫን አይጠበቅባችሁም።
እስከዛሬ ከሞከርኳቸው መንገዶች ይሄ የተሻለና ቀላል ነው። ይህን ነገር አንዴ ካስተካከላችሁ በኋላ ምናልባት የስልካችሁ እስክሪን ቢሰበር ፋይላችሁን ለማውጣት ይጠቅማችኋል። ግን መጀመርያ ይህን ነገር ማስተካከል አለባችሁ ከተሰበረ በኋላ ብትሞክሩት አይሰራም።
- መጀመርያ ስልካችሁን ከኮምፒውተራችሁ ጋር በኬብል ወይም በተመሳሳይ ዋይፋይ connect አድርጉ።
- zip ፋይሉን extract ካደረጋችሁ በኋላ ፎልደሩን ከፍታችሁት open_a_terminal_here የሚል .bat ፋይል አለ እሱን ክፈቱት።
- cmd window ይከፈትላችኋል መጨረሻ ላይ "scrcpy" ብላችሁ ፃፉና enter በሉት።
- ስልካችሁ ላይ ፈቃድ እንድሰጡት ይጠይቃችኋል ok በሉት።
- always allow from this computer የሚለውን ቼክ ቦክስ on ማድረግ አለባችሁ ምክንያቱም ሌላ ጊዜ ስልካችሁን ስትሰኩ በቀላሉ connect ያደርግላችኋል። ይህም የስልካችሁ እስክሪን ቢሰበር ስታገናኙት አይጠይቃችሁም።
- አሁን ስልካችሁን ኮምፒውተራችሁ ላይ ማየት አለባችሁ።
አንዴ connect ካደረጋችሁ በኋላ የስልካችሁ እስክሪን ቢሰበር እራሱ ሌላ ቀን connect ስታደርጉት ቀጥታ ኮምፒውተራችሁ ላይ ይከፍትላችኋል። በኮምፒውተራችሁ Mouseና keyboard መቆጣጠር ትችላላችሁ።
ሶፍትዌሩን ከቴሌግራም ቻናሌ ላይ ማውረድ ትችላላችሁ። click here
What's Your Reaction?






