ኮምፒውተራችን ላይ windows ስንጭን file የሚጠፋብን ለምንድን ነው?

What is firmware?
ምንም አይነት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ያልተጫነበት አዲስ ኮምፒውተር ብንገዛ በውስጡ ምን ይዟል? ብንከፍተውስ ምን ያሳየናል?
ማንኛውም ኮምፒውተር ከሃርድዌር ቀጥሎ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ የሚጫንበት Firmware የሚባል program አለው።
ይህ program መሰረታዊ ተግባራቸውን ለመቆጣጠር በሃርድዌር ሚሞሪዎች ላይ የተጫነ low-level program ነው።
የሚጫነው read-only memory (ROM) ላይ ስለሆነ ማንኛውም ሰው በቀላሉ modify ማድረግ አይችልም።
Firmware ለሚከተሉት ተግባራት ኃላፊነቱን ይወስዳል።
- ኮምፒውተሩ ሲበራ ሃርድዌሩን ማስጀመርና ለስራ ዝግጁ መሆኑን ማረጋገጥ።
- ሃርድዌሩን ከኦፕሬቲንግ ሲስተሙና ከሌሎች ሶፍትዌሮች ጋር ማገናኘት።
- ስህተቶችን ለማስተካከልና አዲስ ባህሪያትን ለመጨመር እራሱን አፕዴት ማድረግ
Firmware በlow-level language የተፃፈ ነው። ለምሳሌ assembly language ወይም ማሽን ኮድ
ይህ የሆነበት ምክንያት ፈርምዌር ከሃርድዌር ጋር በቀጥታ መገናኘት መቻል ስላለበት እና እነዚህ ቋንቋዎች እንደ C ወይም Java ካሉ ከፍተኛ ደረጃ ቋንቋዎች የበለጠ ለሃርድዌር ቅርብ በመሆናቸው ነው።
ለብዙ ሃርድዌር መሳሪያዎች ትክክለኛ ስራ ፈርምዌር አስፈላጊ ነው ያለ firmware የኮምፒውተሩ ሃርድዌሮች ስራ መጀመር ወይም ከሌሎች መሳሪያዎች ጋር መገናኘት አይችሉም።
የፈርምዌር አይነቶች
- BIOS(Basic Input\Output System):
የኮምፒዩተርን የbooting ሂደት የሚቆጣጠረው ፈርምዌር ነው። ሃርድዌርን የማስጀመር እና ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን የመጫን ሃላፊነት አለበት። - UEFI (Unified Extensible Firmware Interface)
Biosን የሚተካ አዲስ የፈርምዌር አይነት ሲሆን ከBIOS የበለጠ ኃይለኛ እና flexible በመሆኑ ተጨማሪ ፊቸሮችን ይይዛል። ለምሳሌ secure boot - Firmware for network adapters:
የNetwork adapter ፈርምዌሮች የኮምፒውተር ኔትዎርክ ግንኙነቱን የሚቆጣጠሩ ሲሆን የፍጥነት እና የዱፕሌክስ ቅንጅቶችን በኔትወርኩ ላይ ካሉ ሌሎች መሳሪያዎች ጋር ግንኙነት እንዲፈጥሩ ያደርጋሉ። - Firmware for storage devices:
ይህ ደግሞ ኮምፒውተራችን ላይ የተከማቸን መረጃ የመቆጣጠር ሃላፊነት አለበት። የspace አጠቃቀምን ያመቻቻል፣ ስህተቶችን ያስተናግዳል እና ፐርፎርማንሱን ይቆጣጠራል።
What are MBR and GPT
MBR እና GPT የpartition table አይነቶች ሲሆኑ ሃርድድራይቫችን ላይ መረጃን ለማደራጀትና ለመደርደር ይጥቅሙናል።
MBR ረጅም ጊዜ ያስቆጠረና older standard ሲሆን GPT በአንፃሩ አዲስና ዘመናዊው የpartition table አይነት ነው።
MBR 512 byte መጠን ያለው በሃርድድራይቫችን መጀመርያ ላይ ሲገኝ በውስጡም ሃርድድራይቭ ፓርትሽኑ እንዴት እንደተደራጀ፣ የፓርትሽኑን አይነትና መጠን ወዘተ መረጃ ይዟል። በተመሳሳይ ኮምፒውተሩ ሲከፈት ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ እንዲነሳ የሚያደርገውን boot loaderም ይይዛል።
MBR የቆየ በመሆኑ ገደብ(limitation) አሉበት።
ለምሳሌ
በአንድ ሃርድድራይቭ ላይ የሚፈቅደው የፓርትሽን ብዛት እስከ 4 ብቻ ነው። ይህም ትልልቅ መጠን ያላቸውን ሃርድ ድራይቮች ወይም ከአራት በላይ ክፍልፍሎች ላሉት ድራይቮች የማይመች ያደርገዋል።
- እያንዳንዱ ክፍልፋይ (partition) እስከ 2 ቴራባይት መጠን ይኖረዋል።
- የሚቀበለው የfirmware interface አይነት ደግሞ BIOS ነው።
GPT(GUID Partition Table)
GPT ዘመናዊ የPartition Table አይነት ሲሆን MBR ያሉበትን ክፍተቶች ይሞላል።
እያንዳንዱ ፓርትሽን ልዩ የሆነ መለያ ይሰጠዋል ይህም ያልተገደበ የፓርትሽን ቁጥር እንዲኖረው ያደርጋል። ኢያንዳንዱ ፓርትሽንም እስከ 8 exabyte ዳታ መያዝ ይችላል።
- GPT ለአብዛኛዎቹ አዳዲስ ኮምፒውተሮች የሚመረጥ ሲሆን ከmbr የተሻለ flexible ነው።
- corruption መቋቋም ይችላል።
- ብዙ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞችን boot ማድረግ ይችላል።
- የሚቀበለው የfirmware interface አይነት UEFI ነው።
ብዙ ጊዜ ኮምፒውተራችን ላይ windows ለመጫን ስንሞክር unable to load on this drive እያለ ፓርትሽኑ ላይ ለመጫን ያስቸግረናል።
ይህም የሚሆንበት ምክንያት ኮምፒውተራችን Bios, mbr ሆኖ ፍላሻችንን ግን በGPT boot ካደረግነው ወይም በተቃራኒው ካደረግነው ነው።
እንደሚታወቀው BIOS firmware interface MBR partition table አለው UEFI ደግሞ GPT
⚠️ እዚጋ መረዳት ያለብን ነገር አንድን ኮምፒውተር ከmbr ወደ gpt ወይም ከgpt ወደ mbr ስንቀይር ሃርድዲስኩ ውስጥ ያለውን ፋይል ሙሉ በሙሉ ያጠፋዋል። ፋይሉን ሳናጠፋ መቀየር አንችልም። እዚጋ ነው ብዙ ሰው ዊንዶውስ ሲጭን ፋይሉ የሚጠፋበት። so ኮምፒውተራችንን windows ከመጫናችን በፊት ሃርድዲስካችን ያለውን የፓርትሽን አይነት አውቀን በተመሳሳይ የፓርትሽን አይነት ፍላሻችንንም boot ማድረግ አለብን።
ኮምፒውተራችን ያለውን የፓርትሽን አይነት ለማዎቅ
- This pc ላይ right click አድርገን manage የሚለውን አንመርጣለን።
- ከሚከፍትልን ውስጥ storage ከሚለው ስር Disk management የሚለውን እንመርጣለን።
- ከተዘረዘሩት ፓርትሽኖች ላይ disk 0 የሚለው ጋ right click አድርገን properties የሚለውን እንመርጣለን።
- Volumes የሚለውን Tab ስንመርጥ ኮምፒውተራችን gpt ወይም mbr መሆኑን ያለውን የፓርትሽን አይነት ያሳየናል።
Windows 11 support የሚያደርገው UEFI ስለሆነ boot ማድረግ የምንችለው በGPT ብቻ ነው። ኮምፒውተራችን bios ሆኖ በGPT boot የተደረገ windows ለመጫን ብንፈልግ አንችልም። መጀመርያ BIOS ወደ UEFI መቀየር ይኖርብናል።
በዚህ አጋጣሚ windows 10 እና windows 11 ለመጫን ኮምፒውተራችን ሊኖረው የሚገባ minimum requirment ምን ምን እንደሆነ እንይ
Windows 10 | Windows 11 | |
Processor | 1 GHz or faster processor | 1GHz or faster with 2 or more cores on a compatible 64-bit processor |
Memory | 1GB RAM for 32-bit or 2GB RAM for 64-bit | 4GB RAM |
Storage | 16GB for 32-bit or 32GB for 64-bit | 64GB or larger storage device |
System Firmware | BIOS or UEFI | UEFI and Secure Boot capable |
TPM(Trusted Platform Module) | Not Required | TPM version 2.0 (This is not a must) |
What's Your Reaction?






