Samsung አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተካተተበትን አዲሱን የS24 series smart ስልክ በይፋ መሸጥ ጀመረ።

Samsung አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተካተተበትን አዲሱን የS24 series smart ስልክ በይፋ መሸጥ ጀመረ።
Samsung አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተካተተበትን አዲሱን የS24 series smart ስልክ በይፋ መሸጥ ጀመረ።

Samsung አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተካተተበትን አዲሱን የS24 series smart phone በይፋ launch አድርጓል።

የስልክ አምራቹ ኩባንያ አዲሱ ምርቱ"All new mobile experience powered by AI" በማለት ይፋ ሲያደርግ S24, S24+, S24 Ultra የሚል ስያሜ ሰትጦታል።
በCounterpoint ጥናት መሰረት ኩባንያው ከዓለም አቀፉ የስማርትፎን ገበያ 20 በመቶ ድርሻ ያለው ሲሆን አፕል 16 በመቶ ድርሻ አለው። በአሜሪካ ገበያ ላይ ግን በአፕል የሚበለጠው ሳምሰንግ አፕል 53% ሳምሰንግ ደግሞ 25% ድርሻ ይይዛሉ። በአሜሪካ ምድር ላይ አዳዲስ ደምበኞችን ለመሳብና የተወሰደበትን የገበያ ብልጫ ለመመለስ iPhone ላይ የሌሉ አዳዲስ ፊቸሮችን ጨምሮ እንደሚመጣ ይጠበቃል።
አዲሱ ስልኩ ምን አልባት Galaxy S24, Galaxy S24+ ወይም Galaxy S24 Ultra የሚል ስያሜ ሊሰጠው እንደሚችል የተገመተ ሲሆን የQualcommን Snapdragon Series 8 Gen 3 ቺፕ ይጠቀማል።
Qualcomm በጥቅምት ወር እንዳስታወቀው አዲሱ የSnapdragon ቺፖች ጄኔሬቲቭ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አፕሊኬሽኖችን ስልኮች ላይ እንድንጠቀም ያስችላቸዋል። በዚህም እንደ ChatGPT አይነት አፕሊኬሽኖችን ያለinternet connection እንዲሰሩ ሊፈቅድ ይችላል።

Series Price
Samsung Galaxy S24 $799
 Samsung Galaxy S24 $999
Samsung Galaxy S24 Ultra $1,299

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow